1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሟች ቤተሰቦች እስካሁን ፍትህ አላገኘንም ይላሉ

ረቡዕ፣ ሰኔ 6 2010

ሰኔ 7፣2009 ዓም በህንጻው 4ተኛ ፎቅ ላይ ከሚገኝ ከአንድ ትዉልደ ኢትዮጵያዊ መኖሪያ ቤት በተነሳው እሳት የ71 ሰዎች ህይወት አልፏል። ከመካከላቸው ኢትዮጵያውያን እና ኤርትራውያን ይገኙበታል።

https://p.dw.com/p/2zVV1
England Londoner Hochhaus
ምስል Picture alliance/AP Photo/F. Augstein

የግሬንፌል ታወር ቃጠሎ አንደኛ ዓመት


ለንደን ብሪታንያ የሚገኘው ግሬንፌል ታወር በመባል የሚጠራው ባለ24 ፎቅ ህንጻ በእሳት ቃጠሎ እንዳልነበረ ከሆነ፤ ነገ አንድ ዓመት ይሞላዋል። በአደጋው የሞቱት ሰዎች ከዛሬ ምሽት አንስቶ በህንጻው አካባቢ በሚካሄዱ የተለያዩ  ስነ ስርዓቶች እና ዝግጅቶች እንደሚታሰቡ ተዘግቧል። ሰኔ 7፣2009 ዓም በህንጻው 4ተኛ ፎቅ ላይ ከሚገኝ ከአንድ ትዉልደ ኢትዮጵያዊ መኖሪያ ቤት በተነሳው እሳት የ71 ሰዎች ህይወት አልፏል። ከመካከላቸው ኢትዮጵያውያን እና ኤርትራውያን ይገኙበታል። የሟች ቤተሰቦች እስካሁን ፍትህ አላገኘንም ሲሉ ያማርራሉ። የለንደንዋ ወኪላችን ሀና ደምሴ ተከታዩን ዘገባ አጠናቅራለች።

ሀና ደምሴ

ኂሩት መለሰ

ነጋሽ መሐመድ