1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጠ/ሚ አብይ የም/ቤት ገለጻ እና የተቃዋሚ ፓርቲዎች አስተያየት

ማክሰኞ፣ ሰኔ 12 2010

የጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ ትናንት በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በመገኘት በወቅታዊ ፖለቲካዊ፣ ኤኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ጉዳዮች ላይ ሰፊ ገለጻ አድርገዋል። ገለጻቸው የተለያዩ አስተያየቶች ቀርበውበታል።

https://p.dw.com/p/2zsRM
Karte Äthiopien englisch

የተቃዋሚ ፓርቲዎች አስተያየት

ዶክተር አብይ ስልጣን ከተረከቡ ወዲህ ትናንት ለመጀመሪያ ጊዜ በምክር ቤት ባቀረቡት ገለጻ ወቅትም ከእንደራሴዎች ለቀረቡላቸው ጥያቄዎችም ምላሽ ሰጥተዋል። ከሁለት ሰዓት በላይ የቆየውን የጠቅላይ ሚንስትሩ ማብራሪያ አንዳንድ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ታሪካዊ እና የሚበረታታ ሲሉት፣ ሌሎች ከንግግር ያላለፈ እና በተግባር ያልታየ ብለውታል።  

ጌታቸው ተድላ ኃይለጊዮርጊስ

አርያም ተክሌ

አዜብ ታደሰ