የጠ/ሚ ዐብይ ሕዝባዊ መድረክ ቅድመ-ዝግጅት በፍራንክፈርት
ማክሰኞ፣ ጥቅምት 20 2011ማስታወቂያ
" አንድ ሆነን እንነሳ ነገንም እንገንባ " በሚለው የለውጡ ኃይል መሪ ቃል በተዘጋጀው በዚሁ አውሮፓ አቀፍ ታሪካዊ ጉባኤ ኢትዮጵያውያን ዝግጅቱ ለሚከናወንበት ትልቁ የኮሜርዝ ባንክ አሬና ስታዲየም ኪራይ እና የተለያዩ ወጪዎችን ለመሸፈን የተሳካ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃግብር ማካሄዳቸውንም በፍራንክፈርት የኢትዮጵያ ኤምባሲ ጄኔራል ቆንሱል አቶ ምህረተዓብ ሙሉጌታ ለ DW ገልጸዋል:: በጀርመን ነዋሪ የሆኑ ከ 200 በላይ ወጣቶች ዝግጅቱን በበጎ አገልግሎት ለማስተባበር በፈቃደኝነት የተመዘገቡ ሲሆን ከመላው አውሮፓ በመኪና ለሚመጡ ታዳሚዎችም ከ 10 ሺህ በላይ የመኪና ማቆሚያ ስፍራዎች መዘጋጀታቸው ታውቋል ። ዝርዝሩን እንዳልካቸው ፈቃደ አጠናቅሮታል::
እንዳልካቸው ፈቃደ
አዜብ ታደሰ