1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጠ/ሚንስትሩ የፍራንክፈርት ስብሰባ እና አንደምታው

ረቡዕ፣ ጥቅምት 21 2011

ጠ/ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በዛሬው ዕለት በጀርመን ፍራንክፈር ከተማ ላይ ለተሰባሰቡ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያ ንግግር አደርገዋል። ጠ/ሚኒስትሩ ጀርመን ዛሬ ለደረሰችበት የኤኮኖሚ ደረጃ የበቃችው ዜጎቿ ወገባቸውን አሥረው ተስፋ መቁረጥን አባርረው፤ የደረሰባቸውን መከራ ታግሰው ለሀገራቸው አንድ ሆነው በትጋት ስለሠሩ መሆኑን አመልክተዋል።

https://p.dw.com/p/37TcG
Frankfurt Ministerpräsident Äthiopien Abiy Ahmed in Commerzbank-Arena
ምስል DW/T. Waldyes

የጠ/ሚንስትሩ የፍራንክፈርት ስብሰባ እና አንደምታው

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በዛሬው ዕለት በጀርመን ፍራንክፈር ከተማ ላይ ለተሰባሰቡ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያ ንግግር አደርገዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጀርመን ዛሬ ለደረሰችበት የኤኮኖሚ ደረጃ የበቃችው ዜጎቿ ወገባቸውን አሥረው ተስፋ መቁረጥን አባርረው፤ የደረሰባቸውን መከራ ሁሉ ለነገ ሲሉ ታግሰው ለሀገራቸው አንድ ሆነው በትጋት ስለሠሩ መሆኑን አመልክተዋል። ዛሬ በአውሮጳ በሚገኙ ወገኖች ፊት ሲቆሙ በኢትዮጵያ ችግሩም ሆነ ግጭት ጠፍቶ ቢሆን እጅግ ይደሰቱ እንደነበር ያመለከቱት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሁንም ግን ሁለት ነገሮች አሉን ሲሉ ንግግራቸውን ቀጥለዋል። ከዚህም ሌላ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከጀርመን እና ከተለያዩ የአውሮጳ ሃገራት በፍራንክፈርት ኮሜርስ አረና ስታዲየም ለተሰባሰቡት ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያ ባደረጉት ንግግር በኢትዮጵያ የተጀመረው የለውጥ እንቅስቃሴ ጠንክሮ እንደሚቀጥል አመልክተዋል።

ነጋሽ መሀመድ

አዜብ ታደሰ