1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጥምቀት በዓል አከባበር በአዲስ አበባ 

ቅዳሜ፣ ጥር 11 2011

በአዲስ አበባ ከተማ በጃንሜዳ በዓሉ ሲከበር ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ የክልል አስተዳደሮች "እኛን ሊለያዩን እና ሰው መሆናችንን ሊያሳጡን አልተፈጠሩም" ሲሉ ተናግረዋል። ሰው በሰውነቱ ሊከበር እንደሚገባ ለጥምቀት በዓል ታዳሚያን አስረድተዋል።

https://p.dw.com/p/3BqWI
Äthiopien Epiphanie-Fest in Addis Abeba
ምስል DW/Y. Gebreegziabher

የጥምቀት በዓል አከባበር በጃንሜዳ

የጥምቀት በዓል በክርስትና ዕምነት ተከታዮች ዘንድ አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ የኢትዮጵያ ከተሞች ሲከበር ውሏል። ዛሬ በአዲስ አበባ ከተማ በጃንሜዳ በዓሉ ሲከበር ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ የክልል አስተዳደሮች "እኛን ሊለያዩን እና ሰው መሆናችንን ሊያሳጡን አልተፈጠሩም" ሲሉ ተናግረዋል። ሰው በሰውነቱ ሊከበር እንደሚገባ ለጥምቀት በዓል ታዳሚያን አስረድተዋል። በዓሉ በክርስትና ዕምነት ተከታዮች ዘንድ በጉጉት የሚጠበቅ እንደሆነ ታዳምያኑ ይናገራሉ። 
ዮሐንስ ገብረእግዚዓብሔር
እሸቴ በቀለ