1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል
ሳይንስ

የፌስቡክ አሰራር

ረቡዕ፣ ሐምሌ 11 2010

ፌስቡክ እየሰራበት የሚገኘዉ አንዱ ዒላማዉ የዓለም ትልቁ የቪዲዮ ማጋርያ ድረ-ገፅ ማድረግ ነዉ። ዒላማቸዉ ከዩ-ቲዩብም ልቆ መገኘት ነዉ። በርካታ ኢትዮጵያዉያን ፌስቡክን በመጠቀም በፖለቲካም ሆነ በማኅበራዊ ዘርፍ በምስል አልያም በድምፅ አስተያየት አቋማቸዉን ሲገልፁ ይታያል።

https://p.dw.com/p/31iEM
Elfenbeinküste Symbolbild Handynutzung
ምስል Getty Images/AFP/I. Sanogo

«ጥቂት የማይባሉ ኢትዮጵያዉያን መልክቶቻቸዉን በፌስቡክ የቀጥታ ስርጭት ያስተላልፋሉ»


የተለያዩ ድምፆች የተቀላቀሉ ስሜቶች በቁጣ የሚጮኹ በደስታ የሚፈነጥዙ ሰዎች የፖለቲካ ሙግቶች አሁን ደሞ ስፖርታዊ ዉድድሮች  በቀጥታ ስርጭት ወደእጅ ስልካችን ይደርሳሉ። ሰዎች ከእጅ ስልካቸዉ ላይ በሺዎች ለሚቆጠሩ ተመልካቾች የቀጥታ ቪዲዮ ስርጭት ያደርጋሉ፤ ያለ ቴክኖሎጂና ሕግ ገደብ ባሻቸዉ መንገድ ይተነፍሳሉ። ከጥቂት ዓመታት በፊት ቢሆን ኖሮ ይህን ማድረግ የማይታሰብ ነበር። ለፌስ ቡክ ቀጥታ ማሰራጫ አገልግሎት ምስጋና ይግባዉና አንድ የእጅ ስልክ ሁሉን ለማድረግ በቂ ሆንዋል። የፌስቡክ ቀጥታ ስርጭት አገልግሎት ለመጀመርያ ጊዜ ሙከራ ላይ የዋለዉ በነሐሴ ፤ 2015 ዓ.ም እንደነበር ተመልክቶአል። በሚያዝያ 2016 ዓ.ም ደግሞ ሙሉ አገልግሎቱን መስጠት ጀምሮአል። አገልግሎቱ ፌስቡክ ዋንና የቪዲዮ መገኛ ድረ ገጽ የማድረግ ትልሙ ጋር በጥብቅ የተቆራኘ ነዉ። ትልሙ ትልቁን የቪዲዮ ማጋርያ ድረ-ገፅ ዩ-ቲዮብን እስከመቀናቀንም ይደርሳል። የዲጂታል ሞያተኛዉ አሜሪካዊ ሪድዋን እንደሚሉት « ፌስቡክ ለቪዲዮ ልቡ ስስ ነች» ሲሉ ነዉ የሚገልጽዋት።     
« ፌስቡክ  እየሰራበት የሚገኘዉ አንዱ ዒላማዉ የዓለም ትልቁ የቪዲዮ ማጋርያ ድረ-ገፅ ማድረግ ነዉ። ዒላማቸዉ ከዩ-ቲዩብም ልቆ መገኘት ነዉ።  ለዚህም ነዉ የፌስቡክ ስልተ አሰራር የቪዲዮ የሚያደላዉ። በፌስቡክ መነሻ ገፃችን ላይ በጣም በርካታ ቪዲዮችን የምናየዉ በዚህ ሳብያ ነዉ። ቪዲዮቹም በርካታ ተመልካቾችን ያገኛሉ። ይህ የሆነዉ ፌስቡክ ስልተ አሰራሩ ለቪዲዮዎች እንዲያደላና ቅድምያ እንዲሰጥ ስለተደረገ ነዉ። የፊስ ቡክ የቀጥታ ስርጭት መልክት ከፍተና የሆነበት ምክንያት ይኸዉ ነዉ»  
የማኅበራዊ ሚዲያዎች ይህን የቀጥታ ስርጭት ከመጀመራቸዉ በፊት ቪዲዮዉን በቀጥታ ለማሰራጨት የሚያስፈልገዉ፤ ቴክኖሎጂና የመሰረተ ልማት እንኳን በግለሰቦች ደረጃ በሚዲያ ተቋማት ደረጃ እንኳ ለሟሟላት እጅግ እጅግ አዳጋች ነበር።  ለቅንብሩን የድምፅ ማድመጫ ማዕቀፉን በመጫን እንዲከታተሉ እንጋብዛለን። 

DW Shift Social Media und Terroranschläge
ምስል Periscope/Jack Daniels


አዜብ ታደሰ
አክመል ነጋሽ