1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ፕሬዚዳንት ኢሣያስ አፈወርቂ የ3 ቀን ጉብኝት በኢትዮጵያ

ቅዳሜ፣ ሐምሌ 7 2010

ከሁለት ዐሥርተ ዓመት ቆይታ በኋላ የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሣያስ አፈወርቂ አዲስ አበባ ቦሌ አየር ማረፊያ ገብተዋል። በአዲስ አበባ ጠቅላይ ሚንሥትር ዐቢይ አህመድን ጨምሮ የመንግሥት ባለሥልጣናት እንዲሁም የኢትዮጵያን እና የኤርትራን ሰንደቅ ዓላማ የያዙ ሰዎች ለፕሬዚዳንቱና ልዑካቸው አቀባበል አድርገዋል።

https://p.dw.com/p/31RBz
Äthiopien - Ankunft des Präsidenten Isayas Afewerki aus Eritrea
ምስል Y. G. Egziabher

ከሁለት ዐሥርተ ዓመት ቆይታ በኋላ የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሣያስ አፈወርቂ እና ልዑካቸው አዲስ አበባ ቦሌ አየር ማረፊያ ገብተዋል። በአዲስ አበባ ጠቅላይ ሚንሥትር ዐቢይ አህመድን ጨምሮ የመንግሥት ባለሥልጣናት እንዲሁም የኢትዮጵያን እና የኤርትራን ሰንደቅ ዓላማ የያዙ ሰዎች ለፕሬዚዳንቱ አቀባበል አድርገዋል። የኤርትራው ፕሬዚዳንት እና ልዑክን ለመቀበል አደባባይ የወጣው በሺህዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች በጭፈራ እና ሆታ ደስታቸውን ገልጠዋል። ፕሬዚዳንቱን እና ልዑካኑን የያዙ ተሽከርካሪዎች ከቦሌ ወጥተው  በሚጓዙበት ወቅትም ከመንገድ ግራ እና ቀኝ የቆሙ ሰዎች የሁለቱን ሀገራት መሪዎች ስም እየጠሩ ሲያወድሱ ተሰምተዋል። ፕሬዚዳንት ኢሣያስ አፈወርቂ አዲስ አበባ የገቡት ለሦስት ቀናት ይፋዊ የሥራ ጉብኝት ሲኾን በቀጥታ ወደ ብሔራዊ ቤተ-መንግሥት አምርተዋል። በቤተመንግሥቱም አቀባበል ተደርጎላቸዋል። 

ማንተጋፍቶት ስለሺ