1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ጀርመን ለሶርያ የምትሰጠዉን ርዳታ ጨመረች

ሐሙስ፣ መጋቢት 5 2011

ጀርርመን ለሶርያ ልትሰጥ ያሰበችዉን የርዳታ ገንዘብ ወደ 1,44 ቢሊዮብ ይሮ ከፍ ማድረግዋን ገለፀች።ይህ የተነገረዉ ዛሬ በአዉሮጳ ኅብረት ዋና መቀመጫ ብረስልስ ላይ እየተካሄደ ባለዉ ለሶርያ በተጠራዉ ዓለም አቀፍ የለጋሾች ጉባኤ ላይ ነዉ።

https://p.dw.com/p/3F4ha
Brüssel Syrien-Geberkonferenz
ምስል Getty Images/AFP/E. Dunand

ጀርመን በሶርያ ጦርነትና ግጭት ለተጎዱ መልሶ ማቋቋሚያ የምትሰጠዉን እርዳታ መጨመር እንድምትሻ ገለፀች ። ይህ የተነገረዉ ዛሬ በአዉሮጳ ኅብረት ዋና መቀመጫ ብረስልስ ላይ እየተካሄደ ባለዉ ለሶርያ በተጠራዉ ዓለም አቀፍ የለጋሾች ጉባኤ ላይ ነዉ። የጀርመኑ የልማት ሚኒስትር ጌርድ ሙለር በብረስልስ በተካሄደዉ ለሶርያ ዓለም አቀፍ ለጋሾች ጉባኤ ላይ ባደረጉት ንግግር ጀርመን ለሶርያ ልትሰጥ ያሰበችዉን የርዳታ ገንዘብ ወደ 1,44 ቢሊዮብ ይሮ ከፍ ታደርጋለች ብለዋል። ይህ ገንዘብ በሶርያ ለሚገኙ ተረጅዎች እና ከሃገር ዉጭ ለሚገኙ የሶርያ ስደተኞች መርጃ ይዉላል ተብሎአል። በጉባኤዉ ላይ የተሰበሰበዉ ገንዘብ በተለይ ለሶርያዉያን የምግብ እና የሕክምና መገልገያ ቁሳቁሶች መግዣ እንዲሁም ለታዳጊ ሕጻናት ትምህርትና የሞያ ስልጠና ክፍያ ግልጋሉት እንደሚዉል ተመልክቶአል።   

Brüssel Syrien-Geberkonferenz | Federica Mogherini, EU-Außenbeauftragte
ምስል Getty Images/AFP/E. Dunand

አዜብ ታደሰ 

ሸዋዬ ለገሠ