1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ጀርመንና ፈረንሳይ ወዳጅነት ውል ፈረሙ

ማክሰኞ፣ ጥር 14 2011

የጀርመን መራሒተ መንግሥት አንጌላ ሜርክል እና የፈረንሳይ ፕሬዚደንት ኤማኑዌል ማክሮ አዲስ የጀርመን እና ፈረንሳይ ወዳጅነት ውል ተፈራረሙ።  ሁለቱ መሪዎች ዛሬ በጀርመን የአኸን ከተማ የተፈራረሙት ውል ጀርመን እና ፈረንሳይ በጎርጎሪዮሳዊው 1963 ዓም የተፈራረሙትን በግንኙነታቸው ላይ ቁልፍ ሚና የተጫወተውን  የኤሊዜ ስምምነትን የሚያጠናክር ነዉ።

https://p.dw.com/p/3BzRq
Angela Merkel und Emmanuel Macron unterzeichnen den neuen Elysée-Vertrag in Aachen
ምስል picture-alliance/dpa/O. Berg

የጀርመን መራሒተ መንግሥት አንጌላ ሜርክል እና የፈረንሳይ ፕሬዚደንት ኤማኑዌል ማክሮ አዲስ የጀርመን እና ፈረንሳይ ወዳጅነት ውል ተፈራረሙ።  ሁለቱ መሪዎች ዛሬ በጀርመን የአኸን ከተማ የተፈራረሙት ውል ጀርመን እና ፈረንሳይ በጎርጎሪዮሳዊው 1963 ዓም የተፈራረሙትን በግንኙነታቸው ላይ ቁልፍ ሚና የተጫወተውን  የኤሊዜ ስምምነትን የሚያጠናክር  እንደሆን ተገልጿል።  ሜርክል እና ማክሮ አገሮቻቸውን በሚያዋስነው 450 ኪሎ ሜትር ርዝመት ባለው ድንበራቸው የሚካሄደውን የጋራ  ትብብር  ማሳደግ ፍላጎት አላቸው።  በተለይም፣   የአየር ንብረት ለውጥን እና ሽብርተኝ የመሳሰሉ ዓለም አቀፍ ችግሮችን ለመታገል የሚደረገውን ጥረት በተሻለ መንገድ ማስተባበር እንደሚሹ ሜርክል በፍረማው ስነ ስርዓት ላይ ተናግረል።  
« የብዙ ወገኖች ትብብር፣ ብሎም፣  የአየር ንብረት ለውጥን መታገልንም ሆነ፣ የዓለም ንግድ ትብብርን ወይም የተመድን ጨምሮ ለዓለም አቀፍ ተቋማት እውቅና መስጠትን የመሳሰለው ጥረት ሁሉ በዓለም አቀፍ ደረጃ ግፊት አርፎበታል። ሁለተኛው የዓለም ጦርነት ካበቃ ከ74 ዓመት፣ ማለትም ከአንድ ሰው እድሜ በኋላ ካሁን በፊት ተቀባይነት አግኝተው የነበሩ ኩነቶች ዛሬ ጥያቄ ውስጥ ገብተዋል። ይህ በመሆኑም፣ አንደኛ፣ በአውሮጳ ህብረት ውስጥ ጀርመን እና ፈረንሳይ የያዙትን ኃላፊነት እንደአዲስ መመልከት አለብን። ስለዚህ፣ ሁለተኛ የትብብራችንን አቅጣጫ እንዳዲስ መለየት  ይገባናል።  ሶስተኛ፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ በጋራ ርምጃ መውሰድ በሚያስችለን የጋራ ሚና ላይ መግባባት ላይ መድረስ ይኖርብናል።»

አርያም ተክሌ 

አዜብ ታደሰ