1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

"ጋዜጠኝነት አንደበት ነው" - መላኩብርሃኑ

እሑድ፣ ሰኔ 9 2011

በአዲስ አበባ የቴሌቢዥን ፖሊስ ፕሮግራም ብዙዎች ያስታውሱታል። አሁን ደግሞ በአርቲስ ቲቢ በአብይ ጉዳይ የቴሌቢዥን ፕሮግራም አዘጋጅ ነው፤ ጋዜጠኛ መላኩ ብርሃኑ።

https://p.dw.com/p/3JyMT
Journalist Melaku Birhanu
ምስል Privat

ጋዜጠኛ መላኩ ብርሃኑ

መላኩ በአርቲስት ቲቪ ዓብይ ጉዳይ በሚል እንግዶችን አሳታፊ የውይይት ፕሮግራም በማዘጋጀት ይታወቃል። ከዚህ ቀደም በአዲስ ቲቪ የፖሊስ ፕሮግራም አዘጋጅ ነበር። ለ18 ዓመታት በጋዜጠኝነት ሙያ አገልግሏል። በተለያዩ የመገናኛ ብዙኃኖች ውስጥ በሙያውና በኃላፊነት ቦታዎች ላይ ሰርቷል። ጋዜጠኝነት በአጋጣሚ የገባበት ሙያ እንዳልሆነ መላኩ ይናገራል። ሲመኘው የነበረው ሙያ ነበር። የሥነ-ጽሁፍ ፍላጎቱ ወደ ሙያው አስገብቶኛልም ይላል። ጋዜጠኛ ለመሆን የውስጥ ፍላጎት ያስፈልጋል የሚለው መላኩ ብዙ እውነቶችን በጽሁፍ የመግለጽ ችሎታም እንደሆነ ይናገራል። መላኩ የሁለት ልጆች አባትም ነው። የአንድ ሴትና የአንድ ወንድ ልጅ። ተግባቢ መሆኑን እራሱ ስለራሱ ባህሪ ይመሰክራል። በርግጥም ስለራስ መመስከር ከባድ ቢሆንም ይላል መላኩ። ሙሉው ዝግጅት ማገናኛው ላይ ይገኛል

ነጃት ኢብራሂም

አዜብ ታደሰ