1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያ ግጭቶች እና መፍትሄያቸው

እሑድ፣ ሐምሌ 8 2010

የኢትዮጵያ ለውጥ በስኬት ብቻ የተሞላ አይደለም። ባለፉት ሦስት ወራት በኢትዮጵያ እዚህም እዚያም በሚከሰቱ ግጭቶች አደጋዎች እና ሁከቶች ፣የሰዎች ሕይወት መጥፋቱ ንብረት መውደሙ እና የሰዎች መፈናቀል ቀጥሏል። በዚህ ረገድ በኦሮምያ በደቡብ በሶማሊያ እና በቤንሻንጉል ክልሎች የደረሱትን መጥቀስ ይቻላል።

https://p.dw.com/p/31SqO
Äthiopien Somalia Vertriebene Menschen
ምስል DW/B. Girma

የኢትዮጵያ ግጭቶች እና መፍትሄዎቻቸው

ዶክተር አብይ አህመድ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ከተሾሙ ባለፈው ረብዕ አንድ መቶ ቀናት ተቆጥረዋል። በነዚህ ጊዜያት በሀገሪቱ ከዚህ ቀደም ይሆናሉ ተብለው ያልተገመቱ በርካታ ፈጣን ለውጦች ተካሂደዋል። የፖለቲካ እሥረኞችን እና ጋዜጠኞችን እንዲሁም በአሸባሪነት ተጠርጥረው የታያዙ በርካታ ግለሰቦችን በይቅርታ በመፍታት የተጀመረው ለውጥ፣በአሸባሪነት ተፈርጀው የነበሩ ተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶችን እና መገናኛ ብዙሀንን ክስ እስከ ማንሳት ፍረጃውንም እስከመሰረዝ ዘልቋል። ከለውጦቹ ውስጥ ትላላቅ እና መለስተኛ የመንግሥት ድርጅቶችን በከፊልም ሆነ በሙሉ ለግል ባለሃብቶች የማዛወር እቅድ ይገኝበታል። ለኢትዮ ኤርትራ የድንበር ግጭት እልባት ለመስጠት የተላለፈው ውሳኔ እና ውሳኔውን ተከትሎም በአጭር ጊዜ ውስጥ ሁለቱ ሀገራት አዲስ ግንኙነት መጀመራቸው ትልቅ ቦታ ከሚሰጣቸው የለውጡ ፍሪዎች ውስጥ አንዱ ነው። ለውጡ ግን በስኬት ብቻ የተሞላ አይደለም። ባለፉት ሦስት ወራት በኢትዮጵያ እዚህም እዚያም በሚከሰቱ ግጭቶች አደጋዎች እና ሁከቶች ፣የሰዎች ሕይወት መጥፋቱ ንብረት መውደሙ እና የሰዎች መፈናቀል ቀጥሏል። በዚህ ረገድ በኦሮምያ በደቡብ በሶማሊያ እና በቤንሻንጉል ክልሎች የደረሱትን መጥቀስ ይቻላል። በኢትዮጵያ የሚካሄዱ ግጭቶች መንስኤዎችና መፍትሄያቸው የዛሬው እንወያይ  ርዕስ ነው። በዚህ ርዕስ ላይ የሚወያዩ ሦስት እንግዶችን ጋብዘናል። እነርሱም አቶ ውብሸት ሙላት የህግ ባለሞያ እና በተለያዩ አገራዊ ጉዳዮች ላይ ለተለያዩ ጋዜጦች እና ዐምደ መረቦች የሚጽፉ ፣ አቶ ዳንኤል መኮንን በወልቂጤ ዩኒቨርስቲ የፖለቲካ ሳይንስ መምህር እንዲሁም ወይዘሮ መስከረም አበራ በዲላ ዩኒቨርስቲ የታሪክ መምህር እና የድረ ገጽ አምደኛ ናቸው። ከታች የሚገኘውን ማገናኛ በመጫን ሙሉውን ውይይት ይከታተሉ።

ኂሩት መለሰ