1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ጠበቃ ሔኖክ አክሊሉ እና አቶ ሚካኤል መላክ ፍርድ ቤት ቀረቡ

ሐሙስ፣ ጥቅምት 8 2011

በፖሊስ ቁጥጥር ሥር የዋሉት ጠበቃ ሔኖክ አክሊሉ እና አቶ ሚካኤል መላክ ፍርድ ቤት ቀረቡ። አራዳ በሚገኘው የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የቀረቡት አቶ ሔኖክ እና አቶ ሚካኤል "የገጠር ሰው አይመራንም በማለት ወጣቶችን አስተባብራችሁ አመጽ ልታነሳሱ ነበር" በሚል መጠርጠራቸውን የሕግ ባለሙያው አቶ ደሙ አስፋው ተናግረዋል።  

https://p.dw.com/p/36n78
Symbolbild Deutschland Justiz
ምስል picture-alliance/dpa/U. Deck

"ወጣቶችን አስተባብራችሁ አመጽ ልታነሳሱ ነበር" በሚል ተጠርጥረዋል

በፖሊስ ቁጥጥር ሥር የዋሉት ጠበቃ ሔኖክ አክሊሉ እና አቶ ሚካኤል መላክ ፍርድ ቤት ቀረቡ። አራዳ በሚገኘው የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የቀረቡት አቶ ሔኖክ እና አቶ ሚካኤል "የገጠር ሰው አይመራንም በማለት ወጣቶችን አስተባብራችሁ አመጽ ልታነሳሱ ነበር" በሚል መጠርጠራቸውን የሕግ ባለሙያው አቶ ደሙ አስፋው ለ«DW» ተናግረዋል።  አቶ ሔኖክን ወክለው በፍር ቤቱ ጥብቅና የቆሙት የሕግ ባለሙያ እንደተናገሩት ከፍልስጤም ኤምባሲ ጋር በመተባበር እስራኤልን መመከት የሚል አጋርነት እና ስልጠና ውስጥ ተሳትፈዋል በሚል ጉዳይ ጭምር መጠርጠራቸውን ገልጸዋል። አቶ ሔኖክ ከዚህ ቀደም በተለያዩ ምክንያቶች ለታሰሩ ሰዎች ጥብቅና በመቆም ይታወቃሉ።  ጠበቃ ሔኖክ በጸረ-ሽብር ሕግ እና የሰብዓዊ መብት ጉዳዮች ላይ በአዳማ ከተማ በሚደረግ የምክክር መድረክ ይሳተፋሉ ተብሎ ይጠበቅ ነበር። ፖሊስ ለምርመራ 15 ቀናት ቢጠይቅም ፍርድ ቤቱ ጉዳዩን ለጥቅምት 15 ቀጠሮ ሰጥቷል።

እሸቴ በቀለ 

ሸዋዬ ለገሠ