1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ፕሬዚደንት ሉላ ዳ ሲልቫ ዳግም ተፈረደባቸዉ

ሐሙስ፣ ጥር 30 2011

የብራዚል ፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት እስር ላይ የሚገኙት የቀድሞዉ የብራዚሊያ ፕሬዚደንት ሉይዝ ኢናሲዮ ሉላ ዳ ሲልቫ ለሁለተኛ ጊዜ በተወነጀሉበት የሙስና ክስ 12 ዓመት ከአስራ አንድ ወር እስራት ተፈረደባቸዉ።  

https://p.dw.com/p/3CwQ3
Brasilien Lula da Silva
ምስል picture-alliance/AP/A. Penner

የብራዚል ፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት እስር ላይ የሚገኙት የቀድሞዉ የብራዚሊያ ፕሬዚደንት ሉይዝ ኢናሲዮ ሉላ ዳ ሲልቫ ለሁለተኛ ጊዜ በተወነጀሉበት የሙስና ክስ 12 ዓመት ከአስራ አንድ ወር እስራት ተፈረደባቸዉ።  የ 72 ዓመቱ የቀድሞዉ የብራዚል ፕሬዚደንት ሉላ ዳ ሲልቫ ለሁለተኛ ጊዜ ችሎት የቀረቡት በተለይ በፈፀሙት ጉቦና ገንዘብ በማጭበርበር ተከሰዉ ነዉ። ሉላ ዳ ሲልቫ በበኩላቸዉ ወንጀሉን አልፈፀምኩም ሲሉ  ጉዳዩ የተቀነባበረ እና ፖለቲካዊ ግብ ያለው ነው ሲሉ ዳግም ተቃዉመዉታል። ጠበቃቸዉም ይግባኝ እንደሚጠይቅ ይፋ አድርጓል።  ቀደም ሲል  ሉላ ዳ ሲልቫ በቀረበባቸው የመጀመርያ የሙስና ክስ 12 ዓመት ተፈርዶባቸዉ ነበር። ዳ ሲልቫ ለብራዚል ፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ባቀረቡት አቤቱታ ጉዳያቸው ሳይታሰሩ ለመከራከር ጠይቀው የነበር ቢሆንም ጥያቅያቸዉ ዉድቅ ሆኖ እስር ላይ ይገኛሉ። የ72 ዓመቱ ግራ ዘመም ፖለቲከኛ ከጎርጎሮሳዊው 2003-2011 ዓ.ም  ባሉት ዓመታት ብራዚልን በፕሬዝዳንትነት አገልግለዋል። በብራዚል በሚካሔደው የአገሪቱ ምርጫም ዳግም ለመወዳደር እቅድ ነበራቸው። ሉላ በሚል የቁልምጫ ስማቸው የሚታወቁት የብራዚሉ ፖለቲከኛ  በርካታ ብራዚላውያን ለደሆች የወገኑ ፖለቲከኛ አድርገው ያደንቋቸዉ ነበር። 

 

አዜብ ታደሰ 

ኂሩት መለሰ