1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ፖለቲካ ፓርቲዎች እና መጪው ምርጫ 

Merga Yonas Bula
ሰኞ፣ ኅዳር 24 2011

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ባለፈዉ ማክሰኞ ከተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች ጋር ዉይይት አድርገዋል። ዉይይቱ መጭዉን ምርጫ ፍትሃዊና ነፃ ለማድረግ ሊወሰዱ የሚገቡ ለዉጦች ላይ ያተኮረ መሆኑን የጠቅላይ ሚኒስትሩ ፅህፈት ቤት ያወጣዉ መረጃ ያመለክታል።

https://p.dw.com/p/39EUn
Äthiopien  - Ministerpräsident Äthiopiens in einer Gesprächsrunde
ምስል Daniel Getachew

በዉይይቱም ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንደ አንደ ስጋት ያነሱት የፖለቲካ ፓርቲዎች ቁጥር መብዛት ነዉ። የፓርቲዎቹ ቁጥር አሁን ካለዉዝቅ ቢል በግላቸዉም ሆነ እንደ ድርጅት ከፍተኛ ድጋፍ እንደሚደረግላቸዉ ቃል ገብተውላቸዋል። 

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የፖለትካ ፓርቲዎች ቁጥር መብዛትን አስመልክቶ ለፓርትዎቹ አመራሮች ያቀረቡትን አስተያየት ወጣቶች እንደት ይመለከቱታል?

የፖለትካ ፓርትዎች ቁጥር መብዛቱን የማይደግፈዉ  የጭሮ ከተማ ነዋሪ ወጣት አም መሃመድ ፣የተለያየ ሃሳብ ቢኖራቸዉም የሚያቀራርቧቸዉ ሃሳቦች ላይ ቢሰሩ ዉጤታማ ይሆናሉም ብለዋል።

አምባቸዉ ደጀነ የሚል የፌስቡክ ስም የያዘ ወጣት ጠ/ሚኒስትሩ «ምን አገባው፣ ለምን ሺ አይሆኑም? ለማን አዝኖ ነው ተጨፍለቁ እያለ የሚመክረው? እነሱ የበዙት ሊቀመንበር ለመሆን የሚፈልጉ ሰዎች ስለበዙ ነው። ሌላ ምንም ምክንያት የላቸውም»፣ ሲል ቀልድና ቁምነገር የተቀላቀለበት አስተያየቱን ሰንዝረዋል። 
ግን ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዉይይቱ ወቅት ሶስት አራት ሁኑ ማለታቸዉ እንደ «ዉሳኔ» ሊታይ እንደማይገባ አስገንዝበዋል።

በሀገሪቱ ዉስጥ ያሉ የፖለትካ ፓርትዎች የተለያየ አቋም በመያዝ ህዝቡን ከሚያንገላቱ እንደ አሜሪካን አጋር አንድ ገዥና አንድ ተቃዋም ቢሆኑ ይመረጣል ያለዉ ደግሞ የጉራጌ ዞን ነዋሪ የሆነዉ ወጣት ደምሴ ሳንኩራ ነዉ።

የፖለቲካ ፓርትዎች ቁጥር ብዙ እንደሆነ የሚናገረው የጅማ ነዋሪው የመልካም አስተዳደር ባለሙያዉ ወጣት ሸሪፍ አባጋላን ግን ወደ ምርጫ ሲመጡ በሚያቀራርባቸዉ ጉዳዮች ላይ ቢቀራረቡና ቢዋሃዱ ብዙ ድምፅ ማግኘት፣ ስልጣንን መሸከምና አጋርን መምራት እንዲችሉ ይረዳቸዋል ሲሉ ለDW ተናግረዋል።

ግንቦት 2012 ዓ/ም ለሚደረገዉ ምርጫ የፖለቲካ ፓርትዎች የግዜ ሰለዳዉ ይራዘም ወይም አይራዝም የሚሉ አስተያየቶች እየሰጡ ነው። 

በተለያዩ አካባቢዎች የሚደርሱ ግጭቶችንና የፖለቲካ አለመረጋጋትን እንዲሁም ፓርቲዎቹ ለምርጫ ዝግጁ አለመሆናቸዉን በመጥቀስ መጪው ምርጫ የሚካሄድበት ጊዜ እንዲራዘም በርካታ የፖለቲካ ፓርቲዎች ከጠየቁ፣ በሌላ ጎራ ደግሞ፣ አይ፣ ምርጫዉን ማራዘም ለሌላ ግጭት መንገድ በር ስለሚከፍት ጊዜዉን ጠብቆ መደረግ አለበት ካሉ፣ መራጩ ወጣትስ በዚህ ጉዳይ ላይ ምን አስተያየት አለው?

ምርጫዉ እንዲራዘም «ሆን ብለዉ ምክንያት የሚፈጥሩ አንዳንድ የፖለቲካ ፓርቲዎች ስላሉ ምርጫዉን ከምራዘም በተያዘለት ጊዜ ቢካሄድ ሲክ የጭሮው ወጣት አምን ይናገራል።

ስማቸዉን ሳይጠቅሱ በDW ዋትስኣፕ ላይ አስተያየታቸዉን ያጋሩን ወጣቶች ደግሞ ይህን ብለዋል፥ «እሰከ አሁን የተካሄዱ ምርጫዎች በሙሉ ፍትሀዊ አልነበሩም፣ ቀጣዩ ምርጫ ቢራዘምም ባይራዘምም ለውጥ አያመጣም፣ ምክንያቱም ምርጫችን አብይ ነው» ብሏል አንድ ወጣት «እሽ፣ እንደኔ የግሌ አስተያየት ምርጫዉ በወቅቱና በጊዜዉ በየአምስት አመቱ እንደተለመደው መደርግ አለበት፣ ምክንያቱም ምርጫዉን ማራዘሙ ግጭት ሊፈጥር እና ህብርተሠቡ ላይስማማ ስለሚችል» ስል ሌላው ሃሳቡን ገልጿል።

ጋድሳ ባርሶ የሚል የፌስቡክ ስም ያለው ግለሰብ «ከምርጫው በፊት በአገሪቱ ላይ ፍፁም ሠላም ሊሆን ይገባል» ብለዋል። ምርጫዉ ሳይደረግ በፊት «ብሔራዊ ዕርቅና ይቅርታ»ን ከሁሉ በፊት ማሰቀደም፣ በለውጡ ያኮረፉትን በፍቅር ማቅረብና ጥያቄያቸውን ማሰተናገድ ፥ የፀጥታና ቀልጣፋ የደህንነት ተቋም መፍጠር እና ሌሎች ላይ መሰራት አለበት ብለዋል። ወድ ባድሜ የሚል ግለሰብ ደግሞ፣ « ከሁሉም የተወጣጣ ግዚያዊ መንግስት ተቋቁሞ የምርጫ ግዜ ይወስን። በጠ/ሚ ኣብይ የሚመራው ኢህኣዴግ ግን ውስጣዊ ኣንድነት የሌለው ብቻ ሳይሆን ኣገራችንን ወደ ለእርሰበርስ ጦርነት እየመራት ነው።»ይላል።

መርጋ ዮናስ

ኂሩት መለሰ