DW Amharic የዓለም ዜና፤ የሚያዝያ 21 ቀን 2016 ዓ.ም ሰኞ
--የአውሮጳ ህብረት ለኢትዮጵያውያን ዜጎች የሚሰጠውን ቪዛ ለመገደብ መወሰኑን ዛሬ አስታወቀ። --በኬንያ ስምጥ ሸለቆ ከተማ አቅራቢያ የሚገኝ አንድ ግድብ ተንዶ በትንሹ 42 ሰዎች ሞቱ። -ቡርኪናፋሶ ወታደራዊ ጁንታ የዶቼ ቬሌን ራድዮ ጨምሮ የተለያዩ ዓለምአቀፍ የዜና ማሰራጫዎችንና ጋዜጦችን ማገዱ አስታወቀ። -የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን የእስራኤል እና የሃማስ ጦርነት ሲያበቃ፤ ከአረብ ሀገራት መሪዎች ጋር በጋዛ ጉዳይ ላይ ለመምከር በሳዑዲ ዋና ከተማ ሪያድ መግባታቸዉ ተዘገበ። ዝርዝሩን ያድምጡ!